መግለጫ መፅሐፍ የታሪካዊ አርኪኦሎጂ ዓውደ-ርዕይ
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ሙዚየም
« ይህ መግለጫ መፅሐፍ፤ የአርኪኦሎጂስቶች፣ የታሪክ ምሁራን፣ የሥነ-ጥበብ ታሪክ አዋቂዎች፣ የጥንታዊ ፅሑፎች ጥናት ባለሞያ (epigraphist)፣እንዲሁም በአፍሪካ ቀንድ የጥንታዊና መካከለኛው ዘመን ታሪክ ተመራማሪዎች ድምር ውጤት ነው። የማህበረሰብ ዓርማ ከሆኑ ቅርጻ-ቅርጾች እስከ ዕለት ተዕለት መጠቀሚያ ቁሶችን ያማከሉ 17 የቅርሶች ስብስብ በዚህ መፅሐፍ ተካተዋል። እነዚህም በዕድሜ ቅደም ተከተል፣ ታሪካዊ ዕሴቶቻቸው እና በኢትዮጵያ የታሪክ ሂደት ውስጥ ጥልቅ ምልከታ እንዲኖር በማስቻል አቅማቸው የተመረጡ፤ ከዋና ዋና መካነ-ቅርስ ቦታዎች የተገኙ ናቸው። የቁሳዊ ቅርሶቹ ብዝኃነት፣ በክህሎት የዳበረ ዕደ-ጥበብ ሞያን፤ የቅርሶቹ በተለያየ መልክዓ-ምድርና ዘመናት መገኘት ድግሞ ያልተገደበ የማህበረሰብ እንቅስቃሴ፣ መድብለ-ባህል፣ ተያያዥነትና የእርስ በእርስ ግንኙንት ነፀብራቅ ናቸው። • • • 1/3 ▶
éditions Soleb
5 rue Guy-de-la-Brosse
75005 Paris
+33 1 47 07 63 33
Isbn 978-2-918157-65-6
Isbn 978-2-918157-67-0
Issn 1639-3465